በምን አይነት አገላልጽ እና የቋንቋ ውቅር ነው የኋላ ታሪኬን መጻፍ ያለብኝ?
Author / Contributor: ሳይ / PSY Editorial Team
ድሮ ልጅ እያለን ስለ ህይወት ታሪካችሁ ጻፉ ስንባል… ከእናቴ ባይተዋር ቢቸና … ከ አባቴ ክፍሌ ሹሉቃ… እድሜዬ ለትምህርት ሲደርስ … እያልን ነበር የምንጽፈው። ግላዊ ድረሰትዎን ከኋላ ህይወታዎ ጋር ለመታረቅ ሲጽፉ “ምን ሆኜ ነበር? ምን አይነት ኑሮ ነው ኖሬ የነበረው? የትናንት ታሪኬ ዛሬዬን እንዴት ቀይሮታል ?ከትናንት ታሪክ ዛሬ ላይ ምን እማራለው” ለሚሉ ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙ እንጂ ታሪኩን ከጻፉ በኋላ ጓደኛን ወይ ቤተሰብን አስነብበው በስነ ጽሁፍ ክህሎት ለማስግረም አይደለም።ስለዚህ እርስዎ ጋር የሚቀር ታሪክ እስከሆነ ድረስ መነሳት ያለባቸው ወሳኝ እና ድብቅ አጋጣሚዎች ጨምሮ ቢፅፉ ይምከራል።
በዝርዝር መጻፍ ውስጤን ስለሚረብሸው ሁሉንም ማስታወስ ይከብዳል ፣ዝም ብዬ ላይ ላዩን ብፅፍስ?
የሰው ልጅ አዕምሮ ከሚድርስበት ስነ ልቦናዊ ጥቃት ራሱን ለመጠበቅ ሁሌ ዝግጁ ነው ። ያልታሰብ መጥፎ አጋጣሚ ባጋጠመው ቁጥር አይምሮ ራሱን ለመክላከል ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ ስለሚሆን ዙርያውን በሙሉ በመጠራጠር ሊደርስበት የሚችልበትን አደጋ በውጥረት እና በጭንቀት መጠበቅ ይጀምራል። ታዲያ በዚህ መልኩ ሊፈጠር የሚችል አደጋን መጠባበቅ ሲጀመሩ ፣ የውስጥ ሰላምዎ ይረበሻል ፣ሰውነትዎ ይሸበራል ፣ ሁኔታው ለ አዕምሮዎም ሆነ ለ አካልዎ በጣም ጎጂ ነው።
ስለዚህ በኋለኛው ህይወትዎ ላይ የተፈጠሩ የህይወት አጋጣዎችን ባሰቡ ቁጥር ንዴት ፣ሃዘን ፣ቂም ፣በቀል ወይ ሃፍረት የሚሰማዎ ከሆነ በእርግጥም በአዕምሮዎ እስካሁን ድረስ በመረብሽ ውስጥ ነው ያለው። ስለዚህ እነኚ የሚረብሹ ትውስታዎች ለምን እንደተፈጠሩ እና አሁን ላይ ያላቸውን ስነ ልቦናዊ ተፅዕኖ እስካላወቁ ድረስ በዚህ መልኩ ሰላም አተው ፣ ስሜትዎ ከ ሃሳብዎ ፣ ሃሳብዎ ከባህሪዎ ጋር ተጣልቶ ያለመፍትሄ ሊኖሩበት የሚችሉበት እድል የሰፋ ነው።ስለዚህ በዝርዘር ዋና ዋና ትውስታዎችን አስከተለው ከሚመጡት ስሜቶች ጋር መጋፈጥ የሚመከር ነገር ነው ።
መጻፍ ምን ያክል አስፈላጊ ነው ?
ፅሁፍ ረቂቅ የሆነ የማሰቢያ መንገድ ነው። ስንጽፍ እናስባለን ፣ማሰባችን ደግሞ ብስሉን ከጥሬ በመለየት ጥሩ ምርጫ ላይ የተመሰረተ ህይወት እንድንኖር ያስችለናል። በኋላ ታሪካችን ላይ የተፈጠሩ ልብ ሰባሪ አጋጣሚዎችን በረቀቀ መንገድ ለማስብ ዝግጁ ካልሆኑ የራስዎትን እንዲሁ የሌሎችን ሰዎች ህይወት ሊያበላሹበት የሚችሉበት እድል የጎላ ነው ።እስከዛሬ ድረስ የኋላ ታሪክ ትውስታዎች አዕምሮው ላይ እየመጡ ያለፍቃድዎ ሲረበሹዎት ነበር ፣ አሁን ግን በገዛ ፍቃድዎ እኚን መጥፎ ትውስታዎች ትኩረት ሰትው ምክንያት እና ውጤታቸውን ሊያስቡ ነው። ሁል ጊዜ ይሚሽሹት የኋለኛ ህይወት ካልዎት አዋጩ መንገድ ዞሮ መጋፈጥ ነው ፣ ጽሁፍ ደግሞ ለዚህ ሁነኛ መፍትሄ ነው።
This article is intended to support personal reflection. It does not replace professional consultation or medical treatment.
Self-Authorship & Narrative Psychology
An autobiographical writing framework based on the Pennebaker Expressive Writing paradigm and clinical narrative consolidation. Designed for systematic self-examination, memory reconsolidation, and moral clarity.
ደህንነት እና አስቸኳይ እርዳታ
ደህንነትዎን መጠበቅ እንደማይችሉ ከተሰማዎት ወይም በአስቸኳይ ችግር ውስጥ ከሆኑ፣ PSY | ሳይ የአስቸኳይ ድጋፍ አይሰጥም። የሚያምኑትን ሰው ያነጋግሩ፣ ወደ ቅርብ የጤና ተቋም ይሂዱ፣ ወይም Ethiopia Lifeline አሁን ይደውሉ።
Call Ethiopia Lifeline: +251 11 662 2222© 2026 ሳይ / PSY · Self-Authorship. All rights reserved.
Pennebaker Expressive Writing Protocol · Clinical Narrative Consolidation